ዘፍጥረት 26:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም፦ “ለምን ወደ እኔ መጣችሁ? እናንተ ጠልታችሁኛል፥ ከእናንተም ለይታችሁ አሳድዳችሁኛል” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅም፣ “ጠልታችሁኝ ካባረራችሁኝ በኋላ፣ አሁን ደግሞ ለምን መጣችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ይስሐቅ “ከዚህ በፊት ጠልታችሁኝ ከአገራችሁ እንድወጣ አድርጋችሁኛል፤ ታዲያ አሁን ልትጐበኙኝ የመጣችሁት ለምንድን ነው?” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም፥ “ለምን ወደ እኔ መጣችሁ? እናንተ ጠልታችሁኛል፤ ከእናንተም ለይታችሁ አሳድዳችሁኛልና” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም፦ ለምን ወደ እኔ መጣችሁ? እናንተ ጠልታችሁኛል ከእናንተም ለይታችሁ አሳድዳችሁኛል አላቸው። |
“‘ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው?’ ብለው የካዱትን፥ ይህን ሙሴን በቁጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።
እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።