Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 26:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ስለዚህ ይስሐቅ “ከዚህ በፊት ጠልታችሁኝ ከአገራችሁ እንድወጣ አድርጋችሁኛል፤ ታዲያ አሁን ልትጐበኙኝ የመጣችሁት ለምንድን ነው?” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ይሥሐቅም፣ “ጠልታችሁኝ ካባረራችሁኝ በኋላ፣ አሁን ደግሞ ለምን መጣችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ይስሐቅም፦ “ለምን ወደ እኔ መጣችሁ? እናንተ ጠልታችሁኛል፥ ከእናንተም ለይታችሁ አሳድዳችሁኛል” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ይስ​ሐ​ቅም፥ “ለምን ወደ እኔ መጣ​ችሁ? እና​ንተ ጠል​ታ​ች​ሁ​ኛል፤ ከእ​ና​ን​ተም ለይ​ታ​ችሁ አሳ​ድ​ዳ​ች​ሁ​ኛ​ልና” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ይስሐቅም፦ ለምን ወደ እኔ መጣችሁ? እናንተ ጠልታችሁኛል ከእናንተም ለይታችሁ አሳድዳችሁኛል አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 26:27
9 Referencias Cruzadas  

ብዙ የበግና የከብት መንጋ፥ እንዲሁም ብዙ አገልጋዮች ስለ ነበሩት ፍልስጥኤማውያን ቀኑበት።


በዚያን ጊዜ አቤሜሌክ ይስሐቅን “ኀይልህ ከእኛ ይልቅ እየበረታ ስለ ሄደ፥ አገራችንን ለቀህ ውጣ” አለው።


እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈጸም አስበናል፤ በዚህም መሠረት ቃል ኪዳን እንድትገባልን የምንፈልገው፥


ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብንና ዘመዶቹን ሁሉ ወደ እርሱ አስመጣቸው፤ እነርሱም በጠቅላላው ሰባ አምስት ሰዎች ነበሩ።


ያ ባልንጀራውን ይደበድብ የነበረው ሰው ሙሴን ወዲያ ገፈተረና ‘አንተን በእኛ ላይ ገዢና ፈራጅ ያደረገህ ማን ነው?


“የእስራኤል ሕዝብ ሙሴን ‘በእኛ ላይ ገዢና ፈራጅ እንድትሆን ያደረገህ ማን ነው?’ በማለት ተቃውመውት ነበር፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይህንኑ ሙሴን በቊጥቋጦው ውስጥ በተገለጠለት መልአክ አማካይነት ገዢና ነጻ አውጪ አድርጎ ወደ እነርሱ ላከው።


“የያዕቆብ ልጆች በወንድማቸው በዮሴፍ ላይ ቀንተው በግብጽ አገር ባሪያ እንዲሆን ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከእርሱ ጋር ነበረ፤


እንግዲህ፥ አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን የሚሉትን እነዚያን ከሰይጣን ማኅበር የሆኑትን ውሸታሞች መጥተው በእግርህ ሥር እንዲወድቁ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኩህም እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ።


ዮፍታሔ ግን “እኔን ጠልታችሁ ከአባቴ ቤት ያባረራችሁኝ እናንተ አይደላችሁምን? ታዲያ አሁን ችግር ሲገጥማችሁ ወደ እኔ መምጣታችሁ ስለምንድነው?” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos