ዘፍጥረት 26:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጉድጓድ አስቈፈረ፥ ስለ እርሷም አልተጣሉም፥ ስምዋንም “ርኆቦት” ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ “አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅም ያን ቦታ ትቶ ሌላ ስፍራ ላይ የውሃ ጕድጓድ አስቈፈረ፤ በዚህ ጊዜ ግን አንድም ሰው ጠብ አላነሣበትም፤ ስለዚህ ያን የውሃ ጕድጓድ፣ “አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጥቶናል፤ እኛም በምድር ላይ እንበዛለን” ሲል ርኆቦት ብሎ ጠራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ የውሃ ጒድጓድ ቈፈረ፤ በዚህኛው የውሃ ጒድጓድ ምክንያት ምንም ጠብ ስላልተነሣ “እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጠን፤ በምድር ላይም እንበዛለን ሲል፥ ያንን ቦታ ‘ረሖቦት’ ” ብሎ ሰየመው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ ቈፈረ፤ ስለ እርስዋም አልተጣሉትም፤ ስምዋንም “መርኅብ” ብሎ ጠራት፤ እንዲህ ሲል፥ “አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፤ በምድርም አበዛን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ አስቋፈረ ስለ እርስዋም አልተጣሉም፤ ስምዋንም፥ ርኖቦት ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን በምድርም እንበዛለን። |