ዘፍጥረት 26:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ ቈፈረ፤ ስለ እርስዋም አልተጣሉትም፤ ስምዋንም “መርኅብ” ብሎ ጠራት፤ እንዲህ ሲል፥ “አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፤ በምድርም አበዛን።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ይሥሐቅም ያን ቦታ ትቶ ሌላ ስፍራ ላይ የውሃ ጕድጓድ አስቈፈረ፤ በዚህ ጊዜ ግን አንድም ሰው ጠብ አላነሣበትም፤ ስለዚህ ያን የውሃ ጕድጓድ፣ “አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጥቶናል፤ እኛም በምድር ላይ እንበዛለን” ሲል ርኆቦት ብሎ ጠራው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጉድጓድ አስቈፈረ፥ ስለ እርሷም አልተጣሉም፥ ስምዋንም “ርኆቦት” ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ “አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ የውሃ ጒድጓድ ቈፈረ፤ በዚህኛው የውሃ ጒድጓድ ምክንያት ምንም ጠብ ስላልተነሣ “እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጠን፤ በምድር ላይም እንበዛለን ሲል፥ ያንን ቦታ ‘ረሖቦት’ ” ብሎ ሰየመው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ አስቋፈረ ስለ እርስዋም አልተጣሉም፤ ስምዋንም፥ ርኖቦት ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን በምድርም እንበዛለን። Ver Capítulo |