ዘፍጥረት 25:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእርሻው ቦታ አብርሃም ከሒታውያን ላይ የገዛው ነው፤ ከዚያም አብርሃም ከሚስቱ ሣራ ጋር ተቀበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የዕርሻ ቦታ አብርሃም ከኬጢያውያን የገዛው ነበር፤ ከሚስቱ ከሣራ አጠገብ በዚያ ተቀበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም አብርሃም ከሒታውያን ላይ የገዛው የመቃብር ቦታ ነው፤ በዚህ ዐይነት አብርሃም ሚስቱ ሣራ በተቀበረችበት ዋሻ ተቀበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም አብርሃም ከኬጢ ልጆች የገዛው እርሻ ነው፤ አብርሃምንና ሚስቱን ሣራን በዚያ ቀበሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ከኬጢ ልጆች የገዛው እርሻ ይህ ነው አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ። |
አብርሃምም ከኤፍሮን ጋር ተስማማ፥ በሒታውያንም ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል በነጋዴዎች ሚዛን ልክ መዝኖ አብርሃም ለኤፍሮን ሰጠው፥ ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ።
በዚህ ዓይነት ከመምሬ በስተ ምሥራቅ ማክፌላ የተባለው የዔፍሮን ቦታ የአብርሃም ርስት ሆነ፤ ይህም ቦታ እርሻውን፥ በውስጡ ያለውን ዋሻና በእርሻው ክልል ውስጥ ያለውን ዛፍ ሁሉን፤
በእርሻው ዳር ያለውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻውን ይስጠኝ፥ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንተ ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንዲሰጠኝ አድርጉልኝ።”