አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ገባና፦ “ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፥ ለውሺውም፥ እንጎቻም አድርጊ” አላት።
ዘፍጥረት 24:67 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም ወደ እናቱ ወደ ሣራ ድንኳን አገባት፥ ርብቃንም ወሰዳት፥ ሚስትም ሆነችው፥ ወደዳትም፥ ይስሐቅም ከእናቱ ሞት ተጽናና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅም ርብቃን ወደ እናቱ ወደ ሣራ ድንኳን ይዟት ገባ፤ አገባት፣ ሚስትም ሆነችው፤ እርሱም ወደዳት። ይሥሐቅም ከእናቱ ሞት ተጽናና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ይስሐቅ እናቱ ሣራ ትኖርበት ወደነበረው ድንኳን ርብቃን ይዞአት ገባ፤ ሚስትም ሆነችው፤ ይስሐቅ ርብቃን ወደዳት፤ በእናቱ ሞት ምክንያት ከደረሰበትም ሐዘን በዚህ ሁኔታ ተጽናና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም ወደ እናቱ ቤት ገባ፤ ርብቃንም ወሰዳት፤ ሚስትም ሆነችው፤ ወደዳት፤ ይስሐቅም ስለ እናቱ ስለ ሣራ ተጽናና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም ወደ እናቱ ወደ ሣራ ድንኳን አገባት ርብቃንም ወሰዳት ሚስትም ሆነችው ወደዳትም ይስሐቅም ከእናቱ ሞት ተጽናና። |
አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሣራ ዘንድ ፈጥኖ ገባና፦ “ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፥ ለውሺውም፥ እንጎቻም አድርጊ” አላት።
ወንዶች ልጆቹና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሡ፥ መጽናናትን እንቢ አለ፥ እንዲህም አለ፦ “ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ።” አባቱም እንደዚህ ስለ እርሱ አለቀሰ።
ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፥ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጉር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደ ተምና ሄደ።
ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! አንቀላፍተው ስላሉት፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ሰዎች ደግሞ ልታዝኑ እንደማይገባ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።