ሎሌውም ከጌታው ግመሎች መካከል ዐሥር ግመሎችን ወስዶ፥ ከጌታውም ዕቃ መልካም መልካሙን ይዞ ተነሣ፥ ተነሥቶም ወደ መስጴጦምያ ወደ ናኮር ከተማ ሄደ።
ዘፍጥረት 24:53 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎሌውም የብርና የወርቅ ጌጥ ልብስም አወጣ፥ ለርብቃም ሰጣት፥ የከበረ ስጦታንም ለወንድምዋና ለእናትዋ አቀረበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የወርቅና የብር ጌጣጌጥ፣ እንዲሁም ልብሶች አውጥቶ ለርብቃ ሰጣት፤ ደግሞም ለወንድሟና ለእናቷ ከፍ ያለ ዋጋ ያላቸው ስጦታዎች ሰጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከወርቅና ከብር የተሠሩ ጌጣጌጦችን፥ እንዲሁም ልብስ አውጥቶ ለርብቃ ሰጣት፤ ለወንድምዋና ለእናትዋም በጣም ውድ የሆኑ ስጦታዎችን አውጥቶ ሰጣቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎሌውም የብርና የወርቅ ጌጥ፥ ልብስም አወጣ፤ ለርብቃም ሰጣት፤ ዳግመኛም ለአባቷና ለእናቷ እጅ መንሻ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎሌውም የብርና የወርቅ ጌጥ ልብስም አወጣ፥ ለርብቃም ሰጣት፤ የከበረ ስጦታንም ለወንድምዋና ለእናትዋ አቀረበ። |
ሎሌውም ከጌታው ግመሎች መካከል ዐሥር ግመሎችን ወስዶ፥ ከጌታውም ዕቃ መልካም መልካሙን ይዞ ተነሣ፥ ተነሥቶም ወደ መስጴጦምያ ወደ ናኮር ከተማ ሄደ።
ግመሎቹም ከጠጡ በኋላ እንዲህ ሆነ፥ ሰውዬው ግማሽ ሰቅል የሚመዝን የወርቅ ቀለበት፥ ለእጆችዋም ዐሥር ሰቅል የሚመዘን ጥንድ የወርቅ አምባር አወጣ፥
አባታቸውም ብዙ ስጦታ፥ ብርና ወርቅ፥ የከበረም ዕቃ፥ በይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች ሰጣቸው፤ መንግሥቱን ግን የበኩር ልጁ ስለ ሆነ ለኢዮራም ሰጠ።
በዙሪያቸውም ያሉ ሁሉ በፈቃዳቸው ካቀረቡት መባ ሁሉ በተጨማሪ በእጃቸው፥ በብር ዕቃና በወርቅ፥ በዕቃዎችና በእንስሶችና በውድ ነገሮች አበረታቱአቸው።
ነገር ግን እያንዳንዲቱ ሴት ከጎረቤትዋ በቤትዋም ካለችው ሴት የብር እቃ የወርቅ እቃ ልብስም ትለምናለች፤ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጉታላችሁ፤ ግብፃውያንንም ትበዘብዛላችሁ።”
ሕዝቅያስም ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱንም፥ ብሩንና ወርቁንም፥ ቅመሙንና የከበረውንም ዘይት፥ መሣርያም ያለበትን ቤት ሁሉ፥ በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው፤ በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።