ይህን መናገሩንም ሳይፈጽም እነሆ፥ ሚልካ የወለደችው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በጫንቃዋ ተሸክማ ወጣች፥ ሚልካም የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት ናት።
ዘፍጥረት 24:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባና ባቱኤልም መለሱ እንዲህም አሉ፦ “ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቷል ክፉም በጎም ልንመልስልህ አንችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባና ባቱኤል እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “ነገሩ ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ በዚህም ሆነ በዚያ ምንም ማለት አንችልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባና ባቱኤልም “ይህ ነገር ከእግዚአብሔር የመጣ ስለ ሆነ፥ መከልከል አንችልም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባቱኤልና ላባም መለሱ፤ እንዲህም አሉ፥ “ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶአል፤ ክፉ ወይም በጎ ልንመልስልህ አንችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባና ባቱኤልም መለሱ እንዲህም አሉ፦ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ መጥቶአል ክፉም በጎ፥ ልንመልስልህ አንችልም |
ይህን መናገሩንም ሳይፈጽም እነሆ፥ ሚልካ የወለደችው የባቱኤል ልጅ ርብቃ እንስራዋን በጫንቃዋ ተሸክማ ወጣች፥ ሚልካም የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት ናት።
ጉዳት አደርስብህ ዘንድ ኃይል ነበረኝ፥ ነገር ግን የአባታችሁ አምላክ ትናንት፥ ‘ያዕቆብን ክፉም ሆነ ደግ ነገር እንዳትናገረው ተጠንቀቅ’ ብሎ ነገረኝ።
ይህም የሆነበት ምክንያት ከሴሎ በመጣው በነቢዩ አኪያ አማካይነት ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ጌታ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፤ ንጉሥ ሮብዓምም የሕዝቡን ሐሳብ ችላ በማለት ሳይቀበል የቀረበትም ምክንያት ጌታ ይህን ለውጥ ለማድረግ ስለ ወሰነ ነው።
“ወንድሞቻችሁ በሆኑት በእስራኤላውያን ላይ አደጋ አትጣሉ፤ ሁላችሁም ወደየቤታችሁ ሂዱ፤ ይህ የሆነውም በእኔ ፈቃድ ነው” ብሎ እንዲነግር አዘዘው። እነርሱም ሁሉ ለጌታ ቃል ታዛዦች በመሆን ወደየቤታቸው ተመልሰው ሄዱ።
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ የሚለውን ከቶ በመጽሕፍት አላነበባችሁምን?
እንግዲህ እግዚአብሔር በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመነው ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን ያን ስጦታ ለእነርሱ ከሰጠ፥ እግዚአብሔርን ለመከላከል እችል ዘንድ እኔ ማን ነበርሁ?”