አሁንም የሰውዬውን ሚስት መልስ፥ እርሱ ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፥ ትድናለህም። ባትመልሳት ግን አንተ እንደምትሞት ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንደሚጠፋ በእርግጥ እወቅ።”
ዘፍጥረት 20:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቢሜሌክም በነገታው ማልዶ ተነሣ፥ ባለሟሎቹንም ሁሉ ጠርቶ የሆነውን ነገር ሁሉ ነገራቸው፥ ሰዎቹም እጅግ ደነገጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ማለዳ፣ አቢሜሌክ ሹማምቱን ሁሉ ጠርቶ፣ የሆነውን ሁሉ ነገራቸው፤ እነርሱም ታላቅ ፍርሀት ዐደረባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ጠዋት በማለዳ አቤሜሌክ ባለሟሎቹን ጠርቶ የሆነውን ነገር ሁሉ በተረከላቸው ጊዜ ደነገጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሜሌክም በጥዋት ተነሣ፤ ብላቴኖቹንም ሁሉ ጠራ፤ ይህንም ነገር ሁሉ በጆሮአቸው ተናገረ፤ ቤተ ሰዎቹም ሁሉ እግዚአብሔርን እጅግ ፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቢሜሌክም በነገታው ማለደ፥ ባሪያዎቹንም ሁሉ ጠራ ይህንንም ነገር ሁሉ በጆሮአቸው ተናገረ ስዎቹም እጅግ ፈሩ። |
አሁንም የሰውዬውን ሚስት መልስ፥ እርሱ ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፥ ትድናለህም። ባትመልሳት ግን አንተ እንደምትሞት ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንደሚጠፋ በእርግጥ እወቅ።”
አቢሜሌክም አብርሃምን ጠርቶ አለው፦ “ይህ ያደረግህብን ምንድነው? ምንስ ክፉ ሠራሁብህ? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ትልቅ ኃጢአት ያመጣህብን ምን ብንበድልህ ነው? ፈጽሞ የማይገባ ነገር በእኔ ፈጸምክብኝ።”