ዘፍጥረት 20:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቢሜሌክም በጎችንና ላሞችን ወንዶችና ሴቶች ባርያዎችን አመጣ፥ ለአብርሃምም ሰጠው፥ ሚስቱን ሣራንም መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አቢሜሌክ፣ በጎችና የቀንድ ከብቶች፣ ወንድና ሴት አገልጋዮችን ለአብርሃም ሰጠው፤ ሚስቱን ሣራንም መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አቤሜሌክ ሣራን ለአብርሃም መልሶ ሰጠው፤ እንዲሁም በጎችና በሬዎች የወንድና የሴት አገልጋዮችም ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሜሌክም አንድ ሺህ ምዝምዝ ብርን በጎችንና ላሞችን፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችን አመጣ፤ ለአብርሃምም ሰጠው፤ ሚስቱን ሣራንም መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቢሜሌክም በጎችንና ላሞችን ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችን አመጣ፤ ለአብርሃምም ስጠው ሚስቱን ሣራንም መለሰለት። |
አሁንም የሰውዬውን ሚስት መልስ፥ እርሱ ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፥ ትድናለህም። ባትመልሳት ግን አንተ እንደምትሞት ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንደሚጠፋ በእርግጥ እወቅ።”
በዚያም ዘመን አቢሜሌክ ከሙሽራው ወዳጅ ከአኮዘትና ከሠራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር አብርሃምን አለው፦ “በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፥