ዘፍጥረት 19:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ ይህን ስፍራ እናጠፋለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና፥ እናጠፋውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰድዶናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ስፍራ ልናጠፋው ነው። በሕዝቦቿ ላይ ወደ እግዚአብሔር የቀረበው ጩኸት ታላቅ በመሆኑ፣ እንድናጠፋት እግዚአብሔር ልኮናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህችን ከተማ ልናጠፋት ነው፤ የእነዚህ ሰዎች ኃጢአት እጅግ መብዛቱን እግዚአብሔር ሰምቶአል፤ ሰዶምንም እንድናጠፋ ልኮናል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛ ይህችን ስፍራ እናጠፋታለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና፤ እናጠፋትም ዘንድ እግዚአብሔር ልኮናል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛ ይህን ስፍራ እናጠፋለንና ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና እናጠፋውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰድዶናል። |
ሁለቱም ሰዎች ሎጥን አሉት፦ “ከዚህ ሌላ ማን አለህ? አማችም ቢሆን ወንድ ልጅም ቢሆን ወይም ሴት ልጅ ብትሆን በከተማይቱ ያለህን ሁሉ ከዚህ ስፍራ አስወጣቸው፥
ጌታም ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኩሰት መታገሥ አልቻለም፤ ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ መሣቀቂያም መረገሚያም ሆናለች ዛሬም እንደሆነ የሚኖርባት የለም።
የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።
“ጌታ እግዚአብሔርን ስላልታዘዝህና የሰጠህን ትእዛዝና ሥርዓት ስላልጠበቅህ እነዚህ ርግማኖች ሁሉ በአንተ ላይ ይመጣሉ፥ እስክትጠፋ ድረስ ያሳድዱህማል፥ ይወርሱሃል።
ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትገቡባት ምድር ፈጥናችሁ እንደምትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ለምስክርነት እጠራለሁ፥ ፈጽሞም ትጠፋላችሁ እንጂ ረጅም ዘመን አትኖሩባትም።
እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች፥ እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ በዘለዓለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።