እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።
ዘፍጥረት 18:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የባሉጥ ዛፎች አጠገብ ተገለጠለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀትር ላይ አብርሃም በመምሬ ትልልቅ ዛፎች አቅራቢያ በምትገኘው ድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር ተገለጠለት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመምሬ የወርካ ዛፎች አጠገብ እግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት፤ የተገለጠለትም በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ከዕለታት አንድ ቀን በቀትር ጊዜ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቀትርም ጊዜ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ ዛፍ ሥር ተገለጠለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቅምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት። |
እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።
አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው፥ እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊ መምሬ የባሉጥ ዛፎች አጠገብ ይኖር ነበር፥ እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።
ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፦ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፥ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፥ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።
ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ መምሬ፥ አብርሃምና ይስሐቅ እንግዶች ሆነው ወደ ተቀመጡባት፥ ወደ ቂርያት-አርባ፥ እርሷም ኬብሮን ወደምትባለው መጣ።
ለባዕድ አገር እያለም በተስፋ ቃል በተሰጠው ምድር፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ወራሾች እንደሆኑት እንደ ይስሐቅና እንደ ያዕቆብ በእምነት በድንኳን ኖረ፤
እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፦ “አንተ ከእኛ ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን?” አለው።