ዘፍጥረት 17:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለብዙ አሕዛብም አባት ትሆናለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ የምገባልህ ኪዳን ይህ ነው፤ የብዙ ሕዝቦች አባት ትሆናለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከአንተ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ የብዙ ሕዝቦች አባት አደርግሃለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ፥ ቃል ኪዳኔን በእኔና በአንተ መካከል አጸናለሁ፤ ለብዙ አሕዛብም አባት ትሆናለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ቃል ኪዳኔ ከአንተ ጋር ነው ለብዙ አሕዛብም አባት ትሆናለህ። |
በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥
ጌታም እንዲህ አላት፥ “ሁለት ሕዝቦች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለቱም ወገኖች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንዱም ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ አገልጋይ ይሆናል።”
እግዚአብሔርም አለው፦ “ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፥ ብዛ፥ ተባዛም፥ ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፥ ነገሥታትም ከጉልበትህ ይወጣሉ።
አባቱም እንዲህ ሲል እንቢታውን ገለጸ፦ “አውቄአለሁ ልጄ ሆይ፥ አውቄአለሁ፥ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል ታላቅም ይሆናል፥ ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፥ ዘሩም የአሕዛብ ሙላት ይሆናል።”
ደግሞም የከነዓንን ምድር፥ በእንግድነት ተቀምጠውበት የነበረውን የእንግድነታቸው ምድር እሰጣቸው ዘንድ ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳኔን መሰረትኩ።