ዘፍጥረት 12:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ሰዎቹን ስለ እርሱ አዘዘ፥ እርሱንም ሚስቱንም ከብቱንም ሁሉ ሸኙአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ፈርዖን ስለ አብራም ለባለሟሎቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም አብራምን ከሚስቱና ከንብረቱ ሁሉ ጋራ አሰናበቱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ባዘዛቸው መሠረት ባለሟሎቹ አብራምንና ሚስቱን ካለው ሀብት ሁሉ ጋር ከአገር አስወጡአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ሰዎቹን ስለ አብራም አዘዘ፤ እርሱንም፥ ሚስቱንም፥ የነበረውንም ሁሉ ሸኙአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ስዎቹን ስለ እርሱ አዘዘ፥ እርሱንም ሚስቱንም ከብቱንም ሁሉ ሸኙአቸው። |