ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ በደልንም ቢሠራ፥ ክፉ ሰው እንደሚያደርገው ርኩሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ታማኝ ባለመሆኑና በሠራው ኃጢአት በእነሱ ይሞታል።
ገላትያ 3:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ሁሉ መከራ የተቀበላችሁት በከንቱ ነውን? እንደዚያ ከሆነ በእርግጥ ከንቱ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ ለከንቱ ከሆነ፣ ይህን ያህል መከራ የተቀበላችሁት እንዲያው ነውን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በወንጌል ምክንያት የተቀበላችሁት መከራ ሁሉ ከንቱ ሆኖ ቀረ ማለት ነውን? ይህን አድርጋችሁ ከሆነ በእርግጥ ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን ያህል መከራ ተቀብላችሁ፥ ለከንቱ አደረጋችሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ከንቱ እንደ ሆነስ እንደዚህ ያለ መከራ በከንቱ ተቀበላችሁን? |
ጻድቁ ግን ከጽድቁ ቢመለስ፥ በደልንም ቢሠራ፥ ክፉ ሰው እንደሚያደርገው ርኩሰት ሁሉ ቢያደርግ፥ በሕይወት ይኖራልን? የሠራው ጽድቅ ሁሉ አይታሰብለትም፤ ታማኝ ባለመሆኑና በሠራው ኃጢአት በእነሱ ይሞታል።