ገላትያ 1:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ሌላ ወንጌል እንዴት ፈጥናችሁ እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በክርስቶስ ጸጋ የጠራችሁን እርሱን ትታችሁ፣ ወደ ተለየ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ መዞራችሁ ደንቆኛል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በክርስቶስ ጸጋ ከጠራችሁ አምላክ እንዲህ ፈጥናችሁ መለየታችሁና ወደ ሌላ ወንጌል ማዘንበላችሁ ያስደንቀኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጸጋዉ የጠራችሁን ክርስቶስን ከማመን ወደ ልዩ ወንጌል እንዴት ፈጥነው እንዳስወጧችሁ አደንቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤ |
ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፥ በከንፈሮቹም ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛል።
ምክንያቱም አንዱ መጥቶ እኛ ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ሆኖ ብታገኙት፥ በመልካምነታችሁ ትታገሡታላችሁ።
የእግዚአብሔርን ቃል ቀላቅለው እንደሚነግዱ እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ በቅንነት ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላክን በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን።
ነገር ግን እነርሱ ከወንጌሉ እውነት ጋር በቅንነት እንዳልሄዱ ባየሁ ጊዜ፥ በሁሉም ፊት ኬፋን እንዲህ አልሁት፦ “አንተ አይሁዳዊ ሆነህ ሳለ እንደ አይሁድ ሳይሆን እንደ አሕዛብ የምትኖር ከሆነ፥ አሕዛብ አይሁድ እንዲሆኑ ለምን ታስገድዳቸዋለህ?”
እንደ ተገለጠልኝም ወጣሁ፤ ምናልባትም በከንቱ እንዳልሮጥ ወይም ሮጬ እንዳልሆን፥ በአሕዛብ መካከል የምሰብከውን ወንጌል፥ በመሪነታቸው ለታወቁት ለብቻቸው አስታወቅኋቸው።
እንደ ሥራችን መጠን ሳይሆን እንደ ራሱ ዕቅድና እንደ ጸጋው መጠን አዳነን፥ በቅዱስም አጠራር ጠራን፤ ይህም ጸጋ ከዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፤