ዕዝራ 8:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ሐሻብያ ከእርሱም ጋር ከሜራሪ ልጆች ወገን የነበረውን ይሻዕያና ወንድሞቹንና ልጆቻቸው ሀያ ወንዶች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ሐሸቢያንና ከሜራሪ ዘሮች የሻያን፣ ከወንድሞቹና ከአጎቶቹ ወንዶች ልጆች ጋራ 20 ወንዶችን አመጡልን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ከመራሪ ጐሣ የሆኑትን ሐሻብያና የሻዕያ ተብለው የሚጠሩትን ሰዎች ቊጥራቸው ኻያ ከሆነ ዘመዶቻቸው ጋር ላኩልን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም አሴብያስን፥ ከእርሱም ጋር ከሜራሪ ልጆች ወገን የነበረውን ኢሳይያስን፥ ሃያውን ወንድሞቹንና ልጆቻቸውን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ሐሸብያን ከእርሱም ጋር ከሜራሪ ልጆች ወገን የነበረውን የሻያንና ሀያውን ወንድሞቹንና ልጆቻቸውን። |
የአምላካችን መልካም እጅ በላያችን ላይ ስለ ነበረች፥ የእስራኤል ልጅ የሌዊ ልጅ ከሆነው ከማሕሊ ልጆች ወገን የነበረውን አስተዋይ ሰው ሼሬብያን፥ ከእርሱም ጋር ዐሥራ ስምንት ልጆቹንና ወንድሞቹን አመጡልን።
ዳዊትና ባለሥልጣኖቹ ሌዋውያንን እንዲያገለግሉ ከመረጧቸው የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ውስጥ ሁለት መቶ ሀያ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችን አመጡ፤ እነዚህም ሁሉ በየሥማቸው ተጠቅሰዋል።