እኔም ንጉሡ አርጤክስስ በወንዝ ማዶ ለምትገኙ ገንዘብ ያዦች ሁሉ፦ የሰማያት አምላክ ሕግ ጸሐፊ የሆነው ካህኑ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ሁሉ በትጋት እንድትሰጡት ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፤
ዕዝራ 7:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስከ መቶ መክሊት ብር፥ እስከ መቶ የቆሬስ መስፈሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶ የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ ዘይት፥ ጨውም የሚፈልገውን ያህል ሳትጽፉ ስጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ አንድ መቶ መክሊት ብር፣ እስከ አንድ መቶ ቆሮስ ስንዴ፣ እስከ አንድ መቶ ባዶስ መስፈሪያ ወይን ጠጅ፣ እስከ አንድ መቶ ባዶስ የወይራ ዘይትና የሚፈለገውን ያህል ጨው ስጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ያኽል የሚመዝን ብር፥ እስከ ዐሥር ሺህ ኪሎ ስንዴ፥ እስከ ሁለት ሺህ ሊትር የወይን ጠጅ፥ እስከ ሁለት ሺህ ሊትር የወይራ ዘይትና የሚያስፈልገውንም ያኽል ጨው ስጡት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከ መቶ መክሊት ብርም ቢሆን፥ እስከ መቶም የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ ዘይት ቢሆን፥ ጨውም ያለ ልክ ቢሆን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስከ መቶ መክሊት ብርም ቢሆን፥ እስከ መቶ የቆሬስ መስፈሪያ ስንዴ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ እስከ መቶም የባዶስ መስፈሪያ ዘይት ቢሆን፥ ጨውም ያለ ልክ ቢሆን ስጡ። |
እኔም ንጉሡ አርጤክስስ በወንዝ ማዶ ለምትገኙ ገንዘብ ያዦች ሁሉ፦ የሰማያት አምላክ ሕግ ጸሐፊ የሆነው ካህኑ ዕዝራ የሚጠይቃችሁን ሁሉ በትጋት እንድትሰጡት ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፤
የዘይቱም ደንብ፥ ከእያንዳንዱ የቆሮስ መስፈሪያ የባዶስን አንድ አሥረኛ ክፍል ትሰጣላችሁ፤ ዐሥር የባዶስ መስፈሪያ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ነውና።
የምታቀርበውን የእህል ቁርባን ሁሉ በጨው ታጣፍጠዋለህ፤ የአምላክህንም የቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቁርባንህ እንዳታጐድል፤ በቁርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ታቀርባለህ።