ዕዝራ 7:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚቀረውን ብርና ወርቅ አንተና ወንድሞችህ እንደ አምላካችሁ ፈቃድ ለማድረግ ደስ የሚላችሁን ነገር አድርጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ የሚቀረውንም ብርና ወርቅ አንተና ወንድሞችህ አይሁድ እንደ አምላካችሁ ፈቃድ ደስ ለሚላችሁ ነገር ሁሉ አውሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ የሚተርፈውንም ብርና ወርቅ እንደ አምላካችሁ ፈቃድ አንተና ወገኖችህ ለምትፈልጉት ነገር እንዲውል አድርግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቀረውም ብርና ወርቅ አንተና ወንድሞችህ ለማድረግ ደስ የሚያሰኛችሁን ነገር እንደ አምላካችሁ ፈቃድ አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቀረውም ብርና ወርቅ አንተና ወንድሞችህ ለማድረግ ደስ የሚያሰኛችሁን ነገር እንደ አምላካችሁ ፈቃድ አድርጉ። |
ስለዚህ በዚህ ገንዘብ ወይፈኖችን፥ አውራ በጎችንና ጠቦቶችን ከእህል ቁርባኖቻቸውና ከመጠጥ ቁርባኖቻቸው ጋር ተግተህ ግዛ፥ በኢየሩሳሌምም ባለው በአምላካችሁ ቤት መሠዊያ ላይ አቅርባቸው።