Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕዝራ 7:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚያ የሚተርፈውንም ብርና ወርቅ እንደ አምላካችሁ ፈቃድ አንተና ወገኖችህ ለምትፈልጉት ነገር እንዲውል አድርግ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚህ የሚቀረውንም ብርና ወርቅ አንተና ወንድሞችህ አይሁድ እንደ አምላካችሁ ፈቃድ ደስ ለሚላችሁ ነገር ሁሉ አውሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የሚቀረውን ብርና ወርቅ አንተና ወንድሞችህ እንደ አምላካችሁ ፈቃድ ለማድረግ ደስ የሚላችሁን ነገር አድርጉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከቀ​ረ​ውም ብርና ወርቅ አን​ተና ወን​ድ​ሞ​ችህ ለማ​ድ​ረግ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኛ​ች​ሁን ነገር እንደ አም​ላ​ካ​ችሁ ፈቃድ አድ​ርጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከቀረውም ብርና ወርቅ አንተና ወንድሞችህ ለማድረግ ደስ የሚያሰኛችሁን ነገር እንደ አምላካችሁ ፈቃድ አድርጉ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 7:18
6 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።


ለእግዚአብሔር ሕግ ወይም ለመንግሥት ሕግ ሁሉ የማይታዘዝ ማንም ሰው ቢኖር በጥንቃቄ እየተመረመረ በሞት ወይም ከሀገር በመባረር ወይም ሀብት ንብረቱን በመወረስ ወይም በእስራት ይቀጣ።”


የሥራው ኀላፊዎች ፍጹም ታማኞች ስለ ሆኑ እነርሱን ስለ ገንዘቡ አወጣጥ መቈጣጠር አያስፈልግም።”


ለሥራው ኀላፊነት የተመረጡትም ሰዎች ፍጹም ታማኞች ስለ ነበሩ ገንዘቡን የሰጡአቸውን ሰዎች አይቈጣጠሩአቸውም ነበር።


ይህም ገንዘብ በጥንቃቄ ሥራ ላይ እንዲውል አድርግ፤ ወይፈኖችን፥ የበግ አውራዎችንና ጠቦቶችን፥ ለመባ የሚሆነውን እህልና የወይን ጠጅ ጭምር በኢየሩሳሌም በተሠራው በአምላክህ ቤተ መቅደስ ውስጥ በሚገኘው መሠዊያ ላይ የሚቀርበውን መባ ሁሉ ግዛበት።


በአምላክህ ቤተ መቅደስ ውስጥ አገልግሎት እንዲከናወንባቸው የተሰጡህን ንዋያተ ቅድሳት በኢየሩሳሌም ለሚመለከው አምላክ አቅርብ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios