እንደ ተጻፉትም ያህል በብዙ ቍጥር ፋሲካን አላከበሩም ነበርና የእስራኤልን አምላክ የጌታን ፋሲካ በኢየሩሳሌም ለማክበር እንዲመጡ ከቤር-ሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ ለእስራኤል ሁሉ አዋጅ እንዲነገር ወሰኑ።
ዕዝራ 7:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንግሥቴ ውስጥ ካሉ ከእስራኤል ሕዝብ፥ ከካህናቱና ከሌዋውያኑም ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ የሚፈልግ ሁሉ ከአንተ ጋር እንዲሄድ አዝዣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናቱንና ሌዋውያኑን ጨምሮ በመንግሥቴ ውስጥ የሚኖርና ከአንተ ጋራ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ የሚፈልግ ማንኛውም እስራኤላዊ መሄድ እንዲችል ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ በማስተዳድረው የንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛት ውስጥ የሚገኙና ከአንተ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ የሚፈልጉ እስራኤላውያን፥ ካህናትና ሌዋውያን ሁሉ እንዲመለሱ ፈቅጃለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንግሥቴም ውስጥ ካሉ ከእስራኤል ሕዝብ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ የሚወድድ ሁሉ ከአንተ ጋር እንዲሄድ አዝዣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንግሥቴ ውስጥ ካሉ ከእስራኤል ሕዝብ ከካህናቱና ከሌዋውያኑም ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ የሚወድድ ሁሉ ከአንተ ጋር እንዲሄድ አዝዣለሁ። |
እንደ ተጻፉትም ያህል በብዙ ቍጥር ፋሲካን አላከበሩም ነበርና የእስራኤልን አምላክ የጌታን ፋሲካ በኢየሩሳሌም ለማክበር እንዲመጡ ከቤር-ሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ ለእስራኤል ሁሉ አዋጅ እንዲነገር ወሰኑ።
ከሕዝቡ ሁሉ ማንም በእናንተ ውስጥ የሚኖር አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፥ እርሱም በይሁዳ ወዳለችው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣ፥ የጌታ የእስራኤል አምላክን ቤት ይሥራ፥ እርሱም በኢየሩሳሌም ያለ አምላክ ነው፤