ዕዝራ 4:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድሪቱም ሕዝብ የይሁዳን ሕዝብ እጅ ያደክሙ ነበር፥ እንዳይገነቡም ያስፈራሯቸው ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የምድሪቱ ነዋሪዎች የይሁዳን ሕዝብ ተስፋ ማስቈረጥና ሥራውንም እንዳይቀጥሉ ማስፈራራት ጀመሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ የምድሪቱ ነዋሪዎች የሆኑት ሕዝቦች አይሁድን በማስፈራራትና ተስፋ ለማስቈረጥ በመሞከር ቤተ መቅደሱን እንዳይሠሩ ሊከለክሉአቸው ተነሣሡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሀገሩም ሕዝብ የይሁዳን ሕዝብ እጅግ ያዳክሙ ነበር፤ እንዳይሠሩም ከለከሉአቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምድሩም ሕዝብ የይሁዳን ሕዝብ እጅ ያደክሙ ነበር፤ እንዳይሠሩም አስፈራሩአቸው፤ |
አለቆቹም ንጉሡን፦ “ይህን የመሰለውን ቃላት እየነገራቸው የሕዝቡን ሁሉ እጅ በዚህችም ከተማ የቀሩትን የወታደሮቹን እጅ እያደከመ ነውና ይህ ሰው እንዲገደል እንለምንሃለን፤ ይህ ሰው ክፋትን እንጂ ለዚህ ሕዝብ ሰላምን አይመኝለትምና” አሉት።