ዕዝራ 4:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም የላኩት የደብዳቤ ግልባጭ ይህ ነው፦ “ለንጉሡ ለአርጤክስስ፥ አገልጋዮችህ በወንዙ ማዶ ያለ አገር የሚኖሩ ሰዎች፤ አሁንም አዲሱ መደበኛ ትርጒም የላኩለት ደብዳቤ ቅጅ ይህ ነው፤ ለንጉሥ አርጤክስስ፣ በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ከሚኖሩት አገልጋዮችህ የተላከ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደብዳቤውም ፍሬ ነገር ይህ ነው፤ በኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ከሚኖሩ አገልጋዮቹ ለንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ የተላከ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለንጉሡ ለአርተሰስታ የላኩት የደብዳቤ ቃልም ይህ ነው፥ “በወንዝ ማዶ ያሉት ሰዎች ባሪያዎችህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለንጉሡ ለአርጤክስስ የላኩት የደብዳቤ ግልባጭ ይህ ነው “በወንዝ ማዶ ያሉት ሰዎች ባሪያዎችህ፤ |
ከአንተ ዘንድ የመጡ አይሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየሩሳሌም እንደመጡ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ዓመፀኛይቱንና ክፉይቱን ከተማ በመስራት፥ ቅጥሮቿንም በማደስ፥ መሠረትዋንም በመጠገን ላይ ናቸው።
የደብዳቤውንም ግልባጭ በወንዝ ማዶ ያለ አካባቢ ገዢ ታትናይ፥ ሽታርቦዝናይና ተባባሪዎቻቸው በወንዙ ማዶ የነበሩ ባለ ሥልጣናት ወደ ንጉሡ ዳርዮስ ላኩለት፤
የጌታን ትእዛዝ ቃልና ለእስራኤል የሆነውን ሥርዓት ይጽፍ ለነበረው ለጸሐፊው ለካህኑ ለዕዝራ ንጉሡ አርጤክስስ የሰጠው የደብዳቤው ግልባጭ ይህ ነው፦
ስለዚህ ሳምራዊቲቱ “አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ?” አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና።