ዕዝራ 2:65 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተጨማሪም ወንዶች አገልጋይዮቻቸውና ሴቶች አገልጋዮቻቸው እነዚህ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ነበሩ ሌላ ሁለት መቶ ወንዶች መዘምራንና ሴቶች መዘምራን ነበሩአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም 7,337 ከሚሆኑት ከወንዶችና ከሴቶች አገልጋዮቻቸው በተጨማሪ ነው፤ 200 ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ነበሯቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይኸውም ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ከነበሩ ከሎሌዎቻቸውና ከገረዶቻቸው ሌላ ሁለት መቶ ወንዶች መዘምራንና ሴቶች መዘምራትም ነበሩአቸው። |
ኤርምያስም ለኢዮስያስ የልቅሶ ግጥም ገጠመለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ሁሉ በልቅሶ ግጥማቸው ስለ ኢዮስያስ ይናገሩ ነበር፤ ይህም በእስራኤል ዘንድ ወግ ሆኖ በልቅሶ ግጥም ተጽፎአል።
ከወንድ አገልጋዮቻቸውና ከሴት አገልጋዮቻቸው ሌላ፥ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ነበሩ፥ ሁለት መቶ አርባ አምስት ወንዶችና ሴቶች መዘምራንም ነበሩአቸው።
ብርንና ወርቅን የከበረውንም የነገሥታትና የአውራጆችን መዝገብ ሰበሰብሁ፥ ወንዶችና ሴቶች አዝማሪዎችን፥ ለሰዎች ልጆች ተድላ የሚሰጡ እጅግ የበዙ ሴቶችንም አከማቸሁ።