ሕዝቅኤል 7:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በክፋት ላይ ክፋት እነሆ፥ ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘መዓት! ተሰምቶ የማይታወቅ መዓት ይመጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “መከራ በመከራ ላይ ይመጣባችኋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ክፋት በክፋት ላይ፤ እነሆ ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ክፉ ነገር፥ አንድ ክፉ ነገር፥ እነሆ፥ ይመጣል። |
እንዲህም በል፦ ‘የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉን ነገር በዚህ ስፍራ ማምጣቴን የሚሰማ ጆሮ ሁሉ ጭው ይልበታል።
በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ አስፈሪ ፍፃሜ ያመጣባቸዋልና።