ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፎች ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርጾችንና የአሼራን ምስሎች አቆሙ፤
ሕዝቅኤል 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም በል፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮች፥ ለኮረብቶች፥ ለምንጮችና ለሸለቆች እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ሰይፍን አመጣባችኋለሁ የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም በል፤ ‘የእስራኤል ተራሮች ሆይ፤ የጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኰረብቶች፤ ለገደላገደሎችና ለሸለቆች እንዲህ ይላል፤ ሰይፍን አመጣባችኋለሁ፤ የማምለኪያ ኰረብቶቻችሁን አጠፋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ተራራዎች የልዑል እግዚአብሔርን ቃል እንዲሰሙ ንገራቸው፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምናገረውን ተራራዎች፥ ኮረብቶችንና ገደላማ ሸለቆዎች ሁሉ ይስሙ፤ ሕዝቦች ለጣዖቶች የሚሰግዱባቸውን ከፍተኛ ቦታዎች ሁሉ የሚያጠፋ ሰይፍ እልካለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእስራኤል ተራሮች የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ በላቸው፤ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች፥ ለምንጮችና ለሸለቆዎች እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ሰይፍን አመጣባችኋለሁ፤ የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም በል፦ የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ ጌታ እግዚአብሔር ለተራሮችና ለኮረብቶች ለምንጮችና ለሸለቆች እንዲህ ይላል፦ እኔ፥ እነሆ፥ እኔ ሰይፍን አመጣባችኋለሁ የኮረብታው መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ። |
ለባዕዳን አማልክትም የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፤ በኮረብታዎች ላይና በዛፎች ጥላ ሥር የሚያመልኩአቸውን የድንጋይ ቅርጾችንና የአሼራን ምስሎች አቆሙ፤
ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፥ ይህም ኃጢአትን የማስወገድ ፍሬ ነው።
“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰብረሻል እስራትሽንም በጥሰሻል፤ አንቺም፦ ‘አላገለግልም’ አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።
ጌታም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፦ “ከዳተኛይቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ወደ ረዘመው ተራራ ሁሉ ከለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች በዚያም አመነዘረች።
የቃል ኪዳኑንም በቀል የሚበቀል ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተሞቻችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ በመካከላችሁም ቸነፈርን እልክባችኋለሁ፤ በጠላትም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ።
የኮረብታ መስገጃዎቻችሁንም አጠፋለሁ፥ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁንም አፈርሳለሁ፥ ሬሳችሁንም በጣዖቶቻችሁ ሬሳዎች ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች።