“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አሳፋሪ ነገር አደረገ፤ ይኸውም ቀድሞ ከነዓናውያን ይፈጽሙት ከነበረው ሁሉ የከፋ ነው፤ በሠራቸውም ጣዖቶች የይሁዳን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፤
ሕዝቅኤል 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ከሕዝቦች ይልቅ በትእዛዛቴ ላይ፥ በዙሪያዋ ካሉ አገሮችም ሁሉ ይልቅ በሕጌ ላይ በክፋቷ አምፃለች፥ እነርሱ ትእዛዛቴን አንቀበልም ብለዋልና፥ በሕጌም አልኖሩምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም በዙሪያዋ ካሉት አገሮችና አሕዛብ ይልቅ በሕጌና በሥርዐቴ ላይ በክፋቷ ዐመፀች፤ ሕጌን ጥላለች፤ ሥርዐቴንም አልተከተለችም።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሩሳሌም ግን ሕጎቼንና ደንቤን በመጣስ ከሌሎች ሕዝቦች ይልቅ የከፋችና በዙሪያዋም ካሉት አገሮች ይበልጥ እምቢተኛ መሆንዋን አሳይታለች፤ ኢየሩሳሌም ሕጎቼንና ደንቦቼን ንቃለች፤ ትእዛዞቼንም አልተከተለችም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ከአሕዛብ ይልቅ ፍርዴን በኀጢአት ለወጠች፤ በዙሪያዋም ከአሉ ሀገሮች ሁሉ ይልቅ ትእዛዜን ተላለፈች፤ ፍርዴን ጥለዋልና፥ በትእዛዜም አልሄዱምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም ከአሕዛብ ይልቅ ፍርዴን በኃጢአት ለወጠች በዙሪያዋም ካሉ አገሮች ሁሉ ይልቅ ትእዛዜን ተላለፈች፥ ፍርዴን ጥለዋልና፥ በትእዛዜም አልሄዱምና። |
“የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አሳፋሪ ነገር አደረገ፤ ይኸውም ቀድሞ ከነዓናውያን ይፈጽሙት ከነበረው ሁሉ የከፋ ነው፤ በሠራቸውም ጣዖቶች የይሁዳን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፤
የይሁዳ ሰዎች ግን ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዦች ሆነው አልተገኙም፤ ይልቁንም ምናሴ እስራኤላውያን ወደ ፊት እየገፉ ሲመጡ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋላቸው ሕዝቦች ይፈጽሙት ከነበረው ይበልጥ ወደ ከፋ ኃጢአት መራቸው።
ቃሌንም ለመስማት እንቢ ወዳሉ ወደ ቀድሞው አባቶቻቸው ኃጢአት ተመለሱ፥ ሊያገለግሉአቸውም እንግዶችን አማልክት ተከተሉ፤ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፈረሱ።
አቤቱ! ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸዋልም ነገር ግን ተግሣጽን ለመቀበል እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ለመመለስ እንቢ አሉ።
እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፤ በትእዛዜ አልሄዳችሁምና፥ ሕጌንም አልፈጸማችሁምና፥ ነገር ግን በዙሪያችሁ እንደሚኖሩት እንደ አሕዛብ ሕግ አድርጋችኋል።
ሰማርያ የኃጢአትሽን ግማሽ አልሠራችም፤ አንቺ ግን ከእነርሱ ይልቅ ርኩሰትሽን አበዛሽ፥ በሥራሽም ርኩሰት ሁሉ እኅቶችሽን ጻድቃን አስመሰልሻቸው።
በእርግጥ በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል፤ የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይደረግ ነው፤ ይኸውም የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው አለ።
አስቀድሞ ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በዝሙት ይለውጣሉ፤ ብቸኛ ንጉሣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።