ሕዝቅኤል 45:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ፥ መቅደሱንም አንጻ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በመጀመሪያው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ፤ መቅደሱንም አንጻው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመጀመሪያው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ምንም ነውር የሌለበት አንድ ወይፈን በመሠዋት ቤተ መቅደሱን ታነጻለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ፤ መቅደሱንም አንጻ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመጀመሪያው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ መቅደሱንም አንጻ። |
ሊያገለግሉኝ ወደ እኔ ለሚቀርቡ ለካህናት፥ ከሳዶቅ ዘር ለሆኑ ለሌዋውያን ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ከደሙ ትወስዳለህ፥ በአራቱ ቀንዶቹ፥ በእርከኑ፥ በአራቱ ማዕዘን ላይ፥ በዙሪያውም ባለው ጠርዝ ላይ ታደርጋለህ፤ እንዲሁ ታነጻዋለህ ታጠራዋለህም።
በሁለተኛውም ቀን ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ነውር የሌለበትን አውራ ፍየል ታቀርባለህ፤ በወይፈኑም እንዳነጹት እንዲሁ መሠዊያውን ያነጹበታል።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጠኛው አደባባይ ፊቱ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ይዘጋ፤ ነገር ግን በሰንበት ቀን ይከፈት እንዲሁም በወር መባቻ ቀን ይከፈት።
ከእስራኤል ልጆች ርኩስነት፥ ከመተላለፋቸውም፥ ከኃጢአታቸውም ሁሉ የተነሣ ለተቀደሰው ስፍራ ያስተሰርይለታል፤ በርኩስነታቸውም መካከል ከእነርሱ ጋር ላለው ለመገናኛው ድንኳን እንዲሁ ያደርጋል።
ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበው የክርስቶስ ደም እንዴት ልቆ፥ ሕያው እግዚአብሔርን ለማምለክ፥ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን!