ሕዝቅኤል 45:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 በየበዓላቱ፥ በየመባቻው፥ በየሰንበታቱ፥ በእስራኤል ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን፥ የመጠጡን መሥዋዕት ማቅረብ በመስፍኑ ላይ ይሆናል፤ እርሱ ለእስራኤል ቤት ሊያስተሰርይ የኃጢአቱን መሥዋዕትና ስጦታውን፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሰላሙን መሥዋዕት ያቀርባል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 በበዓላት፣ በወር መባቻና በሰንበታት፣ ለእስራኤል ቤት በተወሰኑት በዓላት ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን ማቅረብ የገዢው ኀላፊነት ነው፤ ለእስራኤል ቤት ማስተስረያ እንዲሆንም የኀጢአት መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ያቀርባል።’ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 ለሚቃጠለው መሥዋዕት፥ ለእህል ቊርባንና ለመጠጥ ቊርባን በወር መባቻ፥ በሰንበቶች፥ በተወሰኑትም የእስራኤል ሕዝብ በዓላት እንዲቀርቡ የሚያስፈልጉትን ማዘጋጀት የመሪው ግዴታ ነው፤ ለእስራኤላውያን የኃጢአት ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት፥ የእህሉን ቊርባን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነትን ቊርባን ማዘጋጀት አለበት።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 በየበዓላቱም፥ በየመባቻውም፥ በየሰንበታቱም በእስራኤልም ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የመጠጡንም ቍርባን መስጠት በአለቃው ላይ ይሆናል፤ እርሱ ለእስራኤል ቤት ያስተሰርይ ዘንድ የኀጢአቱን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቀርባል።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 በየበዓላቱም በየመባቻውም በየሰንበታቱም በእስራኤልም ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የመጠጡንም ቍርባን መስጠት በአለቃው ላይ ይሆናል፥ እርሱ ለእስራኤል ቤት ያስተሰርይ ዘንድ የኃጢአቱን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅነቱን መሥዋዕት ያቀርባል። Ver Capítulo |