ሕዝቅኤል 45:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሰቅል ሀያ ጌራህ ይሆናል፤ ሀያ ሰቅል፥ ሀያ አምስት ሰቅል እና ዐሥራ አምስት ሰቅል ሲጨመር፥ አንድ ምናን ይሁንላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰቅል ሃያ ጌራህ የሚይዝ ይሆናል፤ በሃያ ሰቅል ላይ ሃያ ዐምስት ሰቅልና ዐሥራ ዐምስት ሰቅል ሲጨመር አንድ ምናን ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሚዛናችሁም፥ ኻያ ጌራህ አንድ ሰቅል፥ ሥልሳ ሰቅል አንድ ምናን ይሁን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰቅሉም ሃያ አቦሊ ይሁን፤ ሃያ ሰቅል፥ ሃያ አምስት ሰቅል፥ ዐሥራ አምስት ሰቅል፥ ምናን ይሁንላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰቅሉም ሀያ አቦሊ ይሁን፥ ሀያ ሰቅል፥ ሀያ አምስት ሰቅል፥ አሥራ አምስት ሰቅል፥ ምናን ይሁንላችሁ። |
በቆጠራው የሚያልፉ ሁሉ ይህን ይስጡ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣል፥ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው፤ ግማሽ ሰቅል ለጌታ ስጦታ ነው።
የምታቀርቡት መባ ይህ ነው፤ ከአንድ ቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ አንድ ስድስተኛ የኢፍ መስፈሪያ፥ ከአንድም ቆሮስ መስፈሪያ ገብስ አንድ ስድስተኛ የኢፍ መስፈሪያ ትሰጣላችሁ።