ሕዝቅኤል 40:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምሥራቅ በኩል ወዳለው ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ በሩንም ለካው፤ መጠኑም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ መግቢያ በሩንም ለካው፤ መጠኑም ከሌሎቹ ጋራ ተመሳሳይ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያም ሰው በምሥራቁ ቅጽር በር በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ ወሰደኝ፤ እርሱም የቅጽሩን በር ሲለካው መጠኑ ልክ እንደ ሌሎቹ ሆኖ አገኘው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውስጠኛውም አደባባይ በምሥራቅ በኩል አገባኝ፤ በሩንም ለካ፤ መጠኑም እንደ እነዚያ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውስጠኛውም አደባባይ በምሥራቅ በኩል አገባኝ፥ እንደዚያውም መጠን በሩን ለካ፥ |