Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 40:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በውስጠኛው አደባባይ በደቡብ በኩል በር ነበረ፤ በደቡብ በኩልም ከበር እስከ በር ድረስ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ውስጠኛው አደባባይ ደግሞ ከደቡብ ጋራ ትይዩ የሆነ በር አለው፤ እርሱም ከዚህ በር አንሥቶ በደቡብ አቅጣጫ እስካለው እስከ ውጭው በር ድረስ ለካው፤ ይህም አንድ መቶ ክንድ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያደርስ ሌላም የቅጽር በር ደግሞ ነበር፤ ያም ሰው ውጪኛውን አደባባይ አቋርጦ አደባባይ እስከዚህ እስከ ሁለተኛው ቅጽር በር ያለውን ስፋት ለካ፤ እርሱም መቶ ክንድ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በደ​ቡብ በኩል በር ነበረ፤ ከበር እስከ በር ድረስ በደ​ቡብ በኩል መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በውስጠኛውም አደባባይ በደቡብ በኩል በር ነበረ፥ ከበር እስከ በር ድረስ በደቡብ በኩል መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 40:27
6 Referencias Cruzadas  

በምሥራቁ በር እንዳለው ዓይነት በሰሜኑ በር ትይዩ ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባ በር ነበር፤ ከአንዱ በር እስከ ሌላው በር አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።


በምሥራቅ በኩል ወዳለው ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ በሩንም ለካው፤ መጠኑም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር፤


ከታችኛው በር ፊት ጀምሮ እስከ ውስጠኛው አደባባይ ፊት ድረስ ወርዱን አንድ መቶ ክንድ አድርጎ ለካ።


አደባባዩንም ለካ፥ ርዝመቱ መቶ ክንድ ወርዱም መቶ ክንድ አራት ማዕዘን ነበር፤ መሠዊያውም በቤቱ ፊት ነበረ።


በሰሜንም ወዳለው በር አመጣኝ፥ እርሱንም ለካው፤ መጠኑም ከሌሎቹ ጋር እኩል ነበር፤


በውስጠኛው መግቢያ በውጭው በኩል በውስጠኛው አደባባይ ለሚዘምሩ ዕቃ ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚመለከት በር አጠገብ ነበረ፥ ወደ ደቡብም ይመለከት ነበር፤ ሌላው ደግሞ ወደ ምሥራቅ በሚመለከተው በር አጠገብ ነበረ፥ ወደ ሰሜን ይመለከት ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios