ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ለዔሳው እንጀራና የምስር ወጥ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዓይነት ዔሳው ብኩርናውን አቃለላት።
ሕዝቅኤል 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም ለራስህ ስንዴና ገብስ፥ ባቄላና ምስር፥ ማሽላና አጃን ውሰድ፥ በአንድ ዕቃ ውስጥ አድርጋቸው፥ ለራስህም ምግብ አዘጋጅ፥ በጎንህ እንደ ምትተኛበት ቀን ቍጥር ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ትበላዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስንዴና ገብስ፣ ባቄላና ምስር እንዲሁም ዘንጋዳና አጃ ወስደህ በአንድ ሸክላ ውስጥ አስቀምጥ፤ ከዚያም ለራስህ እንጀራ ጋግር፤ ሦስት መቶ ዘጠና ቀን በጐንህ በምትተኛበት ጊዜ ትመገበዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሁንም ስንዴና ገብስ፥ ባቄላና ምስር፥ ማሽላና ጠመዥ ውሰድ፤ ሁሉንም በአንድነት ደባልቀህ እንጀራ ጋግር፤ ይህም በግራ ጐንህ በምትተኛባቸው በ 390 ቀኖች ውስጥ የምትመገበው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንተም ስንዴንና ገብስን፥ አተርንና ባቄላን፥ ምስርንና አጃን ወደ አንተ ውሰድ፤ በአንድ ዕቃም ውስጥ አድርገህ እንጀራ ጋግር፤ በጎንህ እንደ ተኛህባት ቀን ቍጥር ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ትበላዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተም ስንዴንና ገብስን ባቄላንና ምስርን ጤፍንና አጃን ወደ አንተ ውሰድ፥ በአንድ ዕቃም ውስጥ አድርገህ እንጀራ ጋግር፥ በጐድንህ እንደ ተኛህበት ቀን ቍጥር ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ትበላዋለህ። |
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ለዔሳው እንጀራና የምስር ወጥ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዓይነት ዔሳው ብኩርናውን አቃለላት።
ደግሞም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ እኔ በኢየሩሳሌም የምግብን በትር እሰብራለሁ፥ ምግብ እየፈሩ በሚዛን ይበላሉ፥ ውኃም እየደነገጡ በልክ ይጠጣሉ፤