ሕዝቅኤል 38:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተዘጋጅ፥ አንተና ወደ አንተ የተሰበሰቡ ጉባኤ ሁሉ ተዘጋጁ፥ አንተም ጠባቂ ሁናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘አንተና በዙሪያህ የተሰበሰቡት ሁሉ ተነሡ፤ ተዘጋጁ፤ አንተም መሪያቸው ሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እንዲዘጋጅ ንገረው፤ ሠራዊቱንም ሁሉ በእርሱ ትእዛዝ ሥር እንዲያዘጋጅ አስታውቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አንተና ወደ አንተ የተሰበሰቡ ወገኖችህ ሁሉ ተዘጋጁ፤ አንተም ራስህን አዘጋጅተህ ጠባቂ ሁናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተና ወደ አንተ የተሰበሰቡ ወገኖችህ ሁሉ ተዘጋጁ፥ አንተም ራስህን አዘጋጅተህ አለቃ ሁናቸው። |
ጌታ ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል አድርጋሃለች፥ በንቀትም ስቃብሃለች፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ስትሸሽ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።
በባቢሎን ቅጥሮች ላይ ዓላማውን አንሡ፥ ጥበቃን አጠናክሩ፥ የጥበቃን ሰዎች አቁሙ፥ ድብቅ ጦር አዘጋጁ፤ በባቢሎን በሚኖሩት ላይ የተናገረውን ጌታ አስቦታልና እንዲሁም ደግሞ አድርጎታልና።