ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የጦርነት ውካታን የማሰማበት ቀኖች ይመጣሉ፥ ይላል ጌታ፤ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፥ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፥ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል ጌታ።
ሕዝቅኤል 26:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሜዳ ያሉት ሴቶች ልጆችዋም በሰይፍ ይገደላሉ። እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መኻል አገር ያሉ ሰፈሮቿም በሰይፍ ይወድማሉ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዋናይቱ ምድር ላይ ባሉት መንደሮች የሚኖሩትንም ሕዝብ በጦርነት በሰይፋቸው ይጨፈጭፋሉ፤ በዚያን ጊዜ ጢሮስ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃለች።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሜዳ ያሉትም ሴቶች ልጆችዋ በሰይፍ ይገደላሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሜዳ ያሉትም ሴቶች ልጆችዋ በሰይፍ ይገደላሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። |
ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የጦርነት ውካታን የማሰማበት ቀኖች ይመጣሉ፥ ይላል ጌታ፤ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፥ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፥ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል ጌታ።
ታላቅ እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር ከአንቺ በስተ ሰሜን የምትቀመጥ ሰማርያ ናት፥ ታናሽ እኅትሽም ከሴቶች ልጆችዋ ጋር ከአንቺ በስተ ደቡብ የምትቀመጥ ሰዶም ናት።
ምርኮአቸውን እመልሳለሁ፤ የሰዶምና የሴቶች ልጆችዋን ምርኮ፥ የሰማርያንና የሴቶች ልጆችዋን ምርኮ፥ በመካከላቸው ያለውን የአንቺንም ምርኮ እመልሳለሁ፥
በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምን እበቀላለሁ፤ እንደ ቁጣዬና እንደ መዓቴ መጠን በኤዶም ላይ ያደርጋሉ፤ በቀሌንም ያውቃሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ስለዚህ እነሆ እጄን በአንተ ላይ ዘርግቻለሁ፥ እንዲበዘብዙህ ለሕዝቦች እሰጥሃለሁ፥ ከሕዝቦች እቆርጥሃለሁ፥ ከአገሮችም እደመስስሃለሁ፤ አጠፋሃለሁም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃለህ።
በሜዳ ያሉትን ሴቶችን ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፤ በአንቺ ላይ ምሽግ ይሠራል፥ ደለልም በአንቺ ላይ ይደለድላል፥ በአንቺም ላይ ጋሻ ያነሣል።