Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 26:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በሜዳ ያሉ​ትም ሴቶች ልጆ​ችዋ በሰ​ይፍ ይገ​ደ​ላሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 መኻል አገር ያሉ ሰፈሮቿም በሰይፍ ይወድማሉ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በሜዳ ያሉት ሴቶች ልጆችዋም በሰይፍ ይገደላሉ። እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በዋናይቱ ምድር ላይ ባሉት መንደሮች የሚኖሩትንም ሕዝብ በጦርነት በሰይፋቸው ይጨፈጭፋሉ፤ በዚያን ጊዜ ጢሮስ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃለች።’ ”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በሜዳ ያሉትም ሴቶች ልጆችዋ በሰይፍ ይገደላሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 26:6
10 Referencias Cruzadas  

ስለ​ዚህ እነሆ በአ​ሞን ልጆች ከተማ በራ​ባት ላይ የሰ​ልፍ ውካ​ታን የማ​ሰ​ማ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለጥ​ፋ​ትም ትሆ​ና​ለች፥ መን​ደ​ሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም የወ​ረ​ሱ​ትን ይወ​ር​ሳል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ታላ​ቂ​ቱም እኅ​ትሽ ከሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ጋር በስተ ግራሽ የም​ት​ቀ​መጥ ሰማ​ርያ ናት፤ ታና​ሽ​ቱም እኅ​ትሽ ከሴ​ቶች ልጆ​ችዋ ጋር በሰተ ቀኝሽ የም​ት​ቀ​መጥ ሰዶም ናት።


እኔ ሕያው ነኝ! አን​ቺና ሴቶች ልጆ​ችሽ እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት እን​ዲሁ ሰዶ​ምና ሴቶች ልጆ​ችዋ አላ​ደ​ረ​ጉም፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ምር​ኮ​አ​ቸ​ው​ንም እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ የሰ​ዶ​ምና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ዋን ምርኮ፥ የሰ​ማ​ር​ያ​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ች​ዋን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ያሉ​ትን የም​ር​ኮ​ኞ​ች​ሽን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ።


በሞ​አ​ብም ላይ በቀ​ልን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ ኤዶ​ም​ያ​ስን እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ እንደ ቍጣ​ዬና እንደ መዓ​ቴም መጠን በኤ​ዶ​ም​ያስ ያደ​ር​ጋሉ፤ በቀ​ሌ​ንም ያው​ቃሉ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በመ​ዓት መቅ​ሠ​ፍ​ትም ታላቅ በቀል አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በቀ​ሌ​ንም በላ​ያ​ቸው በአ​ደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


የአ​ሞ​ንን ከተማ ለግ​መ​ሎች ማሰ​ማ​ሪያ፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች ለመ​ንጋ መመ​ሰ​ጊያ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ስለ​ዚህ እነሆ እጄን ዘር​ግ​ቼ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አስ​በ​ዘ​ብ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም ለይች እቈ​ር​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ከሀ​ገ​ሮ​ችም እደ​መ​ስ​ስ​ሃ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ሃ​ለ​ሁም፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።”


እርሱ በም​ድረ በዳ ያሉ ሴቶች ልጆ​ች​ሽን በሰ​ይፍ ይገ​ድ​ላ​ቸ​ዋል፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ንም በአ​ንቺ ላይ ያስ​ቀ​ም​ጣል፤ በዙ​ሪ​ያ​ሽም ግንብ ይሠ​ራል፤ የጦር መሣ​ሪ​ያም ይዘው ይከ​ቡ​ሻል፤ በጦ​ራ​ቸ​ውም ይወ​ጉ​ሻል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos