ሕዝቅኤል 25:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአሞን ልጆች ጋር ለምሥራቅ ልጆች እከፍታለሁ። ከእንግዲህ ወዲህ የአሞን ልጆች በሕዝቦች መካከል እንዳይታሰቡ ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞዓባውያንንም ከአሞናውያን ጋራ ይገዙላቸው ዘንድ፣ ለምሥራቅ ሕዝብ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ አሞናውያን በአሕዛብ ዘንድ ከእንግዲህ መታሰቢያ አይኖራቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእንግዲህ ወዲህ ዐሞን በመንግሥትነት እንዳትታወቅ ከምሥራቅ የሚመጡ ነገዶች ሞአብንና ዐሞንን እንዲወሩአቸው አደርጋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሞን ልጆች በአሕዛብ መካከል ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰቡ የአሞንን ልጆች ለምሥራቅ ልጆች ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቂርያታይም፥ ከአሞን ልጆች ጋር ለምሥራቅ ልጆች እከፍታለሁ። የአሞን ልጆች በአሕዛብ መካከል ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰቡ ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ። |
ስለዚህ እነሆ ርስት አድርጌ ለምሥራቅ ልጆች አሳልፌ እሰጥሻለሁ፥ እነርሱም በአንቺ ውስጥ ይሰፍራሉ፥ ማደሪያዎቻቸውንም በአንቺ ውስጥ ይሠራሉ፤ ፍሬሽን ይበላሉ ወተትሽንም ይጠጣሉ።
ስለዚህ እነሆ እጄን በአንተ ላይ ዘርግቻለሁ፥ እንዲበዘብዙህ ለሕዝቦች እሰጥሃለሁ፥ ከሕዝቦች እቆርጥሃለሁ፥ ከአገሮችም እደመስስሃለሁ፤ አጠፋሃለሁም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃለህ።