ሕዝቅኤል 20:48 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ጌታ እንዳነደድሁት ሥጋ ለባሽ ሁሉ ያያል፥ እርሱም አይጠፋም በለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንዳነደድሁት ያያል፤ የሚያጠፋውም የለም።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እግዚአብሔር የደቡብን ጫካ በእሳት እንዳያያዝኩትና ማንም ሊያጠፋው እንደማይችል ሁሉም ይመለከታሉ።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም እግዚአብሔር እንዳነደድሁት ሥጋ ለባሽ ሁሉ ያያል፥ እርሱም አይጠፋም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም እግዚአብሔር እንዳነደድሁት ሥጋ ለባሽ ሁሉ ያያል፥ እርሱም አይጠፋም በለው። |
ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፥ አትጠፋምም።’ ”
የዳዊት ቤት ሆይ! ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ስለ ሥራችሁ ክፋት ቁጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣና ማንም ሳያጠፋው እንዳይነድድ፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፥ የተበዘበዘውንም ከጨቋኙ እጅ አድኑ።’
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቁጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይወርዳል፤ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።”
ከቅርንጫፍዋ እሳት ወጣች፥ ፍሬዋንም በላች፥ ለገዢዎች በትረ መንግሥት የሚሆን ብርቱ ቅርንጫፍ በእርሷ ዘንድ የለም። ይህ ሙሾ ነው፥ ለልቅሶም ይሆናል።