ጌታ በስድስት ቀናት ሰማያትንና ምድርን፥ ባሕርን፥ እና በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፤ ስለዚህ ጌታ የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም።
ሕዝቅኤል 20:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰንበታቴንም ቀድሱ፤ እኔም ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ እንድታውቁ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ይሆን ዘንድ ሰንበቴን የተቀደሰ ቀን አድርጉት፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁም ታውቃላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ከእናንተ ጋር ለገባሁት ቃል ኪዳን ምልክት ይሆንላችሁ ዘንድ፥ እንዲሁም እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንኩ ያስታውሳችሁ ዘንድ ሰንበትን የተቀደሰ ቀን አድርጉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰንበታቴንም ቀድሱ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰንበታቴንም ቀድሱ፥ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ይሆናሉ። |
ጌታ በስድስት ቀናት ሰማያትንና ምድርን፥ ባሕርን፥ እና በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፤ ስለዚህ ጌታ የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም።
ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ፥ እግርህን ወደ ሰንበት፥ ሰንበትንም ደስታ፥ ጌታንም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ በራስህ መንገድህን ከመጓዝ፥ ፈቅድህንም ከመፈጸም፥ ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥
“ ‘እኔን ፈጽሞ ብትሰሙ፥ ይላል ጌታ፥ በሰንበትም ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም ባታስገቡ፥ የሰንበትንም ቀን ብትቀድሱ ሥራንም ሁሉ ባትሠሩበት፥
ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፥ አትጠፋምም።’ ”