ኢዮአካዝ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሀያ ሦስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ወር ገዛ፤ እናቱም ሐሙጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፤
ሕዝቅኤል 19:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቦች ስለ እርሱ ሰሙ፤ በጉድጓዳቸው ተያዘ፤ በመንጠቆዎችም ይዘው ወደ ግብጽ ምድር ወሰዱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሕዛብም ስለ እርሱ ሰሙ፤ በጕድጓዳቸውም ገብቶ ተያዘ፤ እነርሱም በስናግ ጐትተው፣ ወደ ግብጽ ምድር ወሰዱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቦች በእርሱ ላይ ጮኹበት በቈፈሩት ጒድጓድም ውስጥ ተያዘ፤ በመንጠቆም አፍንጫውን ሰንገው እየጐተቱ ወደ ግብጽ ወሰዱት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብም ስለ እርሱ ሰሙ፤ እርሱም በጕድጓዳቸው ተያዘ፤ በሰንሰለትም አስረው ወደ ግብፅ ምድር ወሰዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብም ወሬውን ሰሙ እርሱም በጕድጓዳቸው ተያዘ፥ በሰንሰለትም አድርገው ወደ ግብጽ ምድር ወሰዱት። |
ኢዮአካዝ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሀያ ሦስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ወር ገዛ፤ እናቱም ሐሙጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፤
የግብጽም ንጉሥ ወንድሙን ኤልያቄምን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ፥ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው፤ ኒካዑም ወንድሙን ኢዮአክስን ይዞ ወደ ግብጽ ወሰደው።
ስለዚህ ጌታ ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፦ “ ‘ወንድሜ ሆይ! ወዮ! እህቴ ሆይ! ወዮ!’ እያሉ አያለቅሱለትም፥ ወይም፦ ‘ጌታ ሆይ! ወዮ! ግርማዊነቱ ሆይ! ወዮ!’ እያሉ አያለቅሱለትም።