Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 19:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እርሷም ጠበቀች፥ ተስፋዋ እንደ ጠፋ ባየች ጊዜ፥ ከግልገሎችዋ አንዱን ወስዳ ደቦል አንበሳ አደረገችው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ ‘ተስፋዋ መጨናገፉን፣ የጠበቀችውም አለመሳካቱን ባየች ጊዜ፣ ከግልገሎቿ ሌላውን ወስዳ፣ ብርቱ አንበሳ አድርጋ አሳደገችው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የነበራት ዓላማ እንዳልተሳካ አይታ ተስፋ በቈረጠች ጊዜ ከግልገሎችዋ ሌላውን ወስዳ ተንከባክባ በማሳደግ ደቦል አንበሳ አደረገችው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እር​ስ​ዋም ከእ​ር​ስዋ እንደ ወሰ​ዱት ባየች ጊዜ ኀይ​ልዋ ጠፋ፤ ከግ​ል​ገ​ሎ​ች​ዋም ሌላን ወስዳ ደቦል አን​በሳ አደ​ረ​ገ​ችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እርስዋም እንደ ደከመችና ተስፋዋ እንደ ጠፋ ባየች ጊዜ፥ ከግልገሎችዋ ሌላን ወስዳ ደቦል አንበሳ አደረገችው።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 19:5
6 Referencias Cruzadas  

ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፥ ልጄ ሆይ፥ ከአደንህ ወጣህ፥ እንደ አንበሳ አሸመቀ፥ እንደ ሴት አንበሳም አደባ፥ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል?


ሑሻይም በተጨማሪ እንዲህ አለው፥ “አባትህና ሰዎቹ ብርቱ ጦረኞችና ግልገሎችዋም እንደተነጠቁባት የዱር ድብ አምርረው የሚነሡ መሆኑን ታውቃለህ፤ በተጨማሪም አባትህ በጦር ሜዳ ልምድ ያለው ነው፤ ሌሊቱን ከሠራዊቱ ጋር አያድርም፤


ከግልገሎችዋም አንዱን አሳደገችው፥ እርሱም ደቦል አንበሳ ሆነ፥ አደንም ተማረ፥ ሰዎችን በላ።


ሕዝቦች ስለ እርሱ ሰሙ፤ በጉድጓዳቸው ተያዘ፤ በመንጠቆዎችም ይዘው ወደ ግብጽ ምድር ወሰዱት።


እርሱም በአንበሶች መካከል ተመላለሰ፤ ደቦል አንበሳም ሆነ፥ አደንም ተማረ፤ ሰዎችን በላ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos