ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ ወንዶች በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉበትንና ሴቶችም አሼራ ተብላ ለምትጠራው ሴት አምላክ መጋረጃ የሚፈትሉበትን ክፍል ሁሉ ደመሰሰ።
ሕዝቅኤል 16:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከልብሶችሽ ጥቂቱን ወስደሽ የመስገጃ ስፍራዎችሽ ላይ በዝንጉርጉር ልብስ ያስጌጥሻቸውን መስገጆች ለራስሽ ሠራሽ በዚያም ገለሞትሽ፥ እንዲህም ያለ ነገር ከአሁን በፊት አልነበረም፥ ከእንግዲህም ወዲያ አይሆንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከልብስሽ አንዳንዱን ወስደሽ የምታመነዝሪበትን መስገጃ ስፍራ አስጌጥሽበት፤ እንዲህ ዐይነት ነገር ከዚህ ቀደም አልታየም፤ ወደ ፊትም አይኖርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከልብሶችሽ ጥቂቱን ወስደሽ የመስገጃ ስፍራዎችሽን አስጌጥሽባቸው፤ በዚያም አመንዝራነትሽን ቀጠልሽ፤ እነዚህ ድርጊቶች መፈጸም አልነበረባቸውም፤ ከቶም መፈጸም አይገባቸውም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከልብስሽም ወስደሽ በመርፌ የተጠለፉ ጣዖታትን ሠራሽ፤ አመነዘርሽባቸውም፤ ስለዚህ ፈጽመሽ አልገባሽም፤ ከእንግዲህም ወዲህ እንዲህ ያለ ነገር አይሆንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከልብስሽም ወስደሽ በኮረብቶች ላይ በዝንጕርጕር ልብስ ያስጌጥሻቸውን መስገጆች ለራስሽ ሠራሽ በዚያም ገለሞትሽ፥ እንዲህም ያለ ነገር ከአሁን በፊት አልነበረም፥ ከእንግዲህም ወዲያ አይሆንም። |
ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ ወንዶች በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉበትንና ሴቶችም አሼራ ተብላ ለምትጠራው ሴት አምላክ መጋረጃ የሚፈትሉበትን ክፍል ሁሉ ደመሰሰ።
የጌጦቻቸውን ውበት ወደ ትዕቢት ለወጡ፥ የርኩሰታቸውን ምስሎችና አስከፊ ነገሮችን ሰሩባቸው፥ ስለዚህ እኔም ይህንን ለእነርሱ ርኩስ ነገር አደርገዋለሁ።