La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 13:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔ ሳልናገር፦ ጌታ እንዲህ ብሏል ስትሉ፥ ከንቱ ራእይን አላያችሁምን፥ ውሸተኛንም ምዋርት አልተናገራችሁምን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔ ሳልናገር፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” ስትሉ ሐሰተኛ ራእይ ማየታችሁ፣ ውሸተኛስ ትንቢት መናገራችሁ አይደለምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔ ያልተናገርኩትን ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል’ ብላችሁ በምትናገሩበት ጊዜ ሐሰተኛ ራእይን ያያችሁና ሟርትን ያሟረታችሁ አይደለምን?”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔም ሳል​ና​ገር፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ​አል ስትሉ፥ ከንቱ ምዋ​ር​ትን የተ​ና​ገ​ራ​ችሁ፥ የሐ​ሰት ራእ​ይ​ንም ያያ​ችሁ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን?”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔም ሳልናገር፦ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአል ስትሉ፥ ከንቱ ራእይን ያያችሁ ውሸተኛንም ምዋርት የተናገራችሁ አይደላችሁምን?

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 13:7
7 Referencias Cruzadas  

እነሆ እግዚአብሔር እንዳልላከው አወቅሁ፥ በእኔ ላይ ትንቢት የተናገረው ጦቢያና ሰንባላጥ ገዝተውት ስለ ነበረ ነው።


ባለ ራእዮችን፦ “አትመልከቱ” ይላሉ፥ ነቢያትንም፦ “ጣፋጩንና አታላዩን ነገር እንጂ ቅኑን ነገር አትንገሩን፤


ጌታ ሳይልካቸው፦ ጌታ ይላል የሚሉ ሰዎች ከንቱ ነገርንና ውሸተኛ ሟርትን አይተዋል፥ ሆኖም ቃላቸው እንዲፈጸም ይጠብቃሉ።


ነቢዮችዋ ጌታ ሳይናገር “ጌታ እንዲህ ይላል” እያሉ የሐሰት ራእይ በማየትና በውሸት ሟርት፥ በኖራ ይለቀልቋቸዋል።


ተራፊም ትርጒም አልባ ነገር ተናግረዋል፥ ሟርተኞችም ሐሰተኛ ራእይ አይተዋል፤ የሚያሳስቱ ሕልሞችን ተናግረዋል፤ ባዶ ማጽናኛም ሰጥተዋል፤ ለዚህም ነው እረኛም ስለ ሌላቸው እንደ በጎች የተቅበዘበዙትና የተጨነቁት።