ሕዝቅኤል 12:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የምናገረው ቃል ይፈጸማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚዘገይ የለም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከተናገርሁት ቃል ከእንግዲህ የሚዘገይ የለም፤ የምለው ሁሉ ይፈጸማል ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር የምላቸውን ንገራቸው፤ እኔ የተናገርኩት ሁሉ ይፈጸማል፤ ከቶም አይዘገይም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ በላቸው፥ “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የምናገረው ቃል ይፈጸማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚዘገይ የለም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የምናገረው ቃል ይፈጸማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚዘገይ የለም፥ ይላል እግዚአብሔር። |
አንበሳ ከችፍግ ዱሩ ወጥቶአል፥ አሕዛብንም የሚያጠፋ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ለማድረግ ከስፍራው ወጥቶአል፥ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ይሆናሉ።
ከሰይፍም ያመለጡት ጥቂት ሰዎች ከግብጽ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሳሉ፤ በዚያም ለመቀመጥ ወደ ግብጽ ምድር የገቡት የይሁዳ ትሩፍ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማናችን ቃል እንደሚጸና በውኑ ያውቃሉ!
በሕይወት እስካሉ ድረስ ሻጭ ወደሸጠው ነገር አይመለስ፥ ስለ ብዙዎቹ የተነገረው ራእይ አይመለስምና፥ ማንም ሰው በኃጢአቱ ሕይወቱን ማዳን አይችልም።
እንግዲህ ቃሉን እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስታውስ፤ ጠብቀውም፤ ንስሓም ግባ። ባትነቃ ግን እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፤ በማናቸውም ሰዓት እንደምመጣብህ ከቶ አታውቅም።