በዚያም በቤተ መቅደሱ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝብ እጅግ ብዙ ነበር።
ሕዝቅኤል 11:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰይፍ ትወድቃላችሁ፥ በእስራኤልም ድንበር እፈርድባችኋለሁ፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ በዚያ ጊዜም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም በገዛ አገራችሁ ድንበር ላይ በጦርነት ትገደላላችሁ፤ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ በእስራኤልም ተራሮች እፈርድባችኋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰይፍ ትወድቃላችሁ በእስራኤልም ድንበር እፈርድባችኋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። |
በዚያም በቤተ መቅደሱ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝብ እጅግ ብዙ ነበር።
ቀድሞ የእስራኤል ይዞታ የነበረውን በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ ጀምሮ በስተ ደቡብ እስከ ሙት ባሕር የሚገኘውን ግዛት ሁሉ ድል ነሥቶ እንደገና አስመለሰ፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው በጋትሔፌር ተወላጅ አገልጋይ በሆነው በአሚታይ ልጅ በነቢዩ ዮናስ አማካይነት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው።
ነገር ግን የሚመካው፦ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ ጌታ መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኙኝ ነገሮች እነዚህ ናቸውና፥ ይላል ጌታ።”
ኖራ የቀባችሁትን ቅጥር አፈርሳለሁ፥ ወደ ምድርም እጥለዋለሁ፥ መሠረቱም ይታያል። እርሱም ይወድቃል፥ እናንተም በውስጧ ትጠፋላችሁ፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
መሸፈኛዎቻችሁን ደግሞ እቀድዳለሁ፥ ሕዝቤንም ከእጃችሁ አድናለሁ፥ ከዚህ ወዲያ በእጃችሁ ለመታደን አይሆኑም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
ስለዚህ ከዚህ በኋላ ከንቱ ራእይን አታዩም፥ ምዋርትም አታሟርቱም፥ ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
እጄ ከንቱ ራእይን በሚያዩ፥ በውሸትም በሚያምዋርቱ ነቢያት ላይ ትሆናለች፥ እነርሱም በሕዝቤ ማኅበር ውስጥ አይገኙም፥ በእስራኤል ቤት መዝገብ አይጻፉም፥ ወደ እስራኤልም ምድር አይገቡም፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
የጌባላውያንም ምድር፥ በፀሐይም መውጫ በኩል ከአርሞንዔም ተራራ በታች ካለችው በኣልጋድ ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ ያለችው ሊባኖስ ሁሉ፥