Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 11:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከመካከልዋ አወጣችኋለሁ፥ በባዕዳንም እጅ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፥ በላያችሁም ላይ ፍርድ አመጣባችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከከተማዪቱ አውጥቼ ለባዕዳን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ ፍርድንም አመጣባችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እናንተን ከከተማይቱ አስወጥቼ ለባዕዳን ሕዝቦች አሳልፌ በመስጠት እፈርድባችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከመ​ካ​ከ​ል​ዋም አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በባ​ዕ​ዳ​ንም እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በላ​ያ​ች​ሁም ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከመካከልዋም አወጣችኋለሁ፥ በእንግዶችም እጅ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፥ በላያችሁም ፍርድ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 11:9
22 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እኔ ራሴ በአንቺ ላይ ነኝ፥ አገሮችም እያዩ በመካከልሽ ፍርድን አመጣብሻለሁ።


በአሕዛብም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ የሚጠሉአቸውም ገዙአቸው።


“ጌታ አንተን በአንተም ላይ የምታነግሠውን ንጉሥ አንተና አባቶችህ ወደማታውቁት ሕዝብ ይወስዳችኋል። በዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካለህ።


ቤቶችሽን በእሳት ያቃጥላሉ፥ በብዙ ሴቶችም ፊት በላይሽ ፍርድን ያደርጉብሻል፥ አመንዝራነትሽን አስተውሻለሁ፥ ከእንግዲህም በኋላ ዋጋ አትሰጪም።


ይህም በሁሉ ላይ ለመፍረድ ነው፤ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኀጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዐመፀኞችም ኀጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኀጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ”


ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። ክፉ ብታደርግ ግን ፍራ፤ በከንቱ ሰይፍ አይታጠቅምና፤ ቁጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና።


የሰው ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው።


እንግዲህ በግብጽ ላይ ፍርድን አመጣለሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ቁጣዬንም አፈስስብሃለሁ፥ በመዓቴም እሳት አነድብሃለሁ፥ ማጥፋትንም ለሚያውቁ ለጨካኞች ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ።


በአመንዝሮችና በደም አፍሳሽ ሴቶች ላይ የሚፈረደውን ፍርድ እፈርድብሻለሁ፥ የመዓትንና የቅንዓትን ደም አመጣብሻለሁ።


በአንቺ ላይ በንዴትና በቁጣ፥ በመዓትም ዘለፋ ፍርድን ባደረግሁብሽ ጊዜ፥ በዙሪያሽ ላሉ አገሮች መሰደቢያና መተረቻ፥ ማስጠንቀቂያና ድንጋጤ ትሆኛለሽ፥ እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።


ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፥ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፥ ፍርድንም አደርግብሻለሁ፥ ከአንቺም የተረፉትንም ሁሉ ወደ ሁሉም ነፋሳት እበትናለሁ።


የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች ዓይኑ እያየ በሪብላ ገደላቸው፤ የባቢሎንም ንጉሥ የይሁዳን መሳፍንት ሁሉ ገደለ።


በክፉ ሥራ ላይ ፈጥኖ ፍርድ አይበየንምና በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ክፉን መሥራት ጠነከረ።


ፊንሐስም ተነሥቶ ፈረደባቸው፥ ቸነፈሩም ተወ፥


በተለይም ምናሴ የንጹሓን ሰዎችን ደም በማፍሰሱና ኢየሩሳሌምንም በንጹሓን ደም በመሙላቱ ምክንያት ይህ ሁሉ ሊፈጸም ችሎአል፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለምናሴ ምሕረት ሊያደርግለት አልፈቀደም።


ስለዚህ እናንተ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ያፈለስኋችሁ ምርኮኞች ሁሉ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፦


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከልዋ ያኖራችኋቸው የተገደሉት እነርሱ ሥጋው ናቸው፥ ድስቱ ይህች ከተማ ናት፥ እናንተን ግን ከመካከልዋ አወጣችኋለሁ።


ከአባቶቻችን ዘመን ጀምረን እስከ ዛሬ ድረስ በታላቅ በደል ነበርን፤ ዛሬም እንደ ሆነው ስለ ኃጢአታችን እኛ፥ ነገሥታቶችንና ካህናቶቻችን ለሰይፍ፥ ለምርኮ፥ ለብዝበዛና ለእፍረት በምድር ነገሥታት እጅ ተሰጠን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios