ከዚህ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፥ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
ሕዝቅኤል 10:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሕያዋኑ መንፈስ በመንኰራኵሮች ውስጥ ስለ ነበረ እነዚህ ሲቆሙ እነዚያም ይቆሙ ነበር፥ እነዚህ ሲነሱ እነዚያም ከእነርሱ ጋር ይነሱ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኪሩቤል ቀጥ ብለው በሚቆሙበት ጊዜ እነርሱም ደግሞ ይቆማሉ፤ ኪሩቤል ከምድር ከፍ ከፍ በሚሉበት ጊዜ፣ የሕያዋኑ ፍጡራን መንፈስ በውስጣቸው ስላለ፣ መንኰራኵሮችም ዐብረዋቸው ይነሡ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕያዋን ፍጥረቶች መንፈስ በመንኰራኲሮቹ ውስጥ ስላለ ፍጥረቶቹ ሲቆሙ መንኰራኲሮቹም አብረው ይቆማሉ፤ ኪሩቤሉ ሲነሡ መንኰራኲሮቹም ወደ ሌላ አይዞሩም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሕይወት መንፈስ በውስጣቸው ነበርና እነዚህ ሲቆሙ እነዚያም ይቆሙ ነበር፤ እነዚህም ሲበርሩ፥ እነዚያ ከእነርሱ ጋር ይበርሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕይወት ያላቸው የእንስሶች መንፈስ በመንኰራኵሮች ውስጥ ነበረና እነዚህ ሲቆሙ እነዚያ ይቆሙ ነበር፥ እነዚህም ከፍ ከፍ ሲሉ እነዚያ ከእነርሱ ጋር ከፍ ከፍ ይሉ ነበር። |
ከዚህ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፥ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
ኪሩቤልም ሲሄዱ መንኰራኵሮቹ በአጠገባቸው ይሄዱ ነበር፥ ኪሩቤል ከምድር ለመነሣት ክንፎቻቸውን ሲዘረጉ መንኰራኵሮቹም ከአጠገባቸው አይለዩም ነበር።
ይህም የሕያዋኑ ክንፎች እርስ በእርሳቸው ሲማቱ የሚወጣው ድምፅ፥ በአጠገባቸውም የነበሩት የመንኰራኵሮች ድምፅ ነበር፥ እርሱም ታላቅ የሚያጉረመርም ድምፅ ነበር።
ከሦስቱ ቀን ተኩልም በኋላ ከእግዚአብሔር የወጣ የሕይወት መንፈስ ገባባቸው፤ በእግሮቻቸውም ቆሙ፤ ታላቅም ፍርሃት በሚመለከቱት ላይ ወደቀባቸው።