ሕዝቅኤል 10:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኪሩቤልም ሲሄዱ መንኰራኵሮቹ በአጠገባቸው ይሄዱ ነበር፥ ኪሩቤል ከምድር ለመነሣት ክንፎቻቸውን ሲዘረጉ መንኰራኵሮቹም ከአጠገባቸው አይለዩም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኪሩቤል ሲንቀሳቀሱ፣ መንኰራኵሮቹም ከጐናቸው ይንቀሳቀሱ ነበር፤ ኪሩቤልም ከምድር ለመነሣት ክንፋቸውን ሲዘረጉ፣ መንኰራኵሮቹ ከአጠገባቸው አይለዩም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኪሩቤሉ ሲንቀሳቀሱ ከጐናቸው ያሉት መንኰራኲሮችም አብረው ይንቀሳቀሳሉ፤ ኪሩቤሉ ለመነሣት ክንፋቸውን ሲዘረጉ ከጐናቸው ያሉት መንኰራኲሮችም ወደ ሌላ አይዞሩም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኪሩቤልም ሲሄዱ መንኰራኵሮቹ ከእነርሱ ጋር ተያይዘው ይሄዱ ነበር፤ ኪሩቤልም ይበሩ ዘንድ ክንፋቸውን ከምድር በሚያነሡ ጊዜ ከእነርሱ ጋር የተያያዘ መንኰራኵራቸው አይመለስም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኪሩቤልም ሲሄዱ መንኰራኵሮቹ በአጠገባቸው ይሄዱ ነበር፥ ኪሩቤልም ከምድር ከፍ ከፍ ይሉ ዘንድ ክንፎቻቸውን ሲዘረጉ መንኰራኵሮች ደግሞ ከአጠገባቸው ፈቀቅ አይሉም ነበር። |
የሕያዋኑ መንፈስ በመንኰራኵሮች ውስጥ ስለ ነበረ እነዚህ ሲቆሙ እነዚያም ይቆሙ ነበር፥ እነዚህ ሲነሱ እነዚያም ከእነርሱ ጋር ይነሱ ነበር።
ይህም የሕያዋኑ ክንፎች እርስ በእርሳቸው ሲማቱ የሚወጣው ድምፅ፥ በአጠገባቸውም የነበሩት የመንኰራኵሮች ድምፅ ነበር፥ እርሱም ታላቅ የሚያጉረመርም ድምፅ ነበር።