እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ከነሐስ የተሠሩ አራት መንኰራኲሮችና መንኰራኲሮቹ የሚሽከረከሩበት የነሐስ ወስከምቶች ነበራቸው፤ እንዲሁም በአራቱ ማእዘኖች የመታጠቢያ ገንዳ መደገፊያዎች ነበሩ፤ መደገፊያዎቹም የአበባ ጉንጉን በሚመስሉ ቅርጾች አጊጠው ነበር።
ሕዝቅኤል 10:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአራቱም መልክ አንድ ይመስል ነበር፥ በመንኰራኵር ውስጥ እንዳለ መንኰራኵር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአራቱም መልክ ይመሳሰል ነበር፤ እያንዳንዱም መንኰራኵር በመንኰራኵር ውስጥ ተሰክቶ የተሠራ ይመስል ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአራቱ መንኰራኲሮች መልክ ተመሳሳይ ነበር፤ እነርሱም በመንኰራኲር ውስጥ የሚተላለፉ መንኰራኲሮች ይመስሉ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአራቱም መልክ አንድ ይመስል ነበር፤ መልካቸውም በመንኰራኵር ውስጥ እንደ አለ መንኰራኵር ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአራቱም መልክ አንድ ይመስል ነበር፥ መልካቸውም በመንኰራኵር ውስጥ እንዳለ መንኰራኵር ነበር። |
እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ከነሐስ የተሠሩ አራት መንኰራኲሮችና መንኰራኲሮቹ የሚሽከረከሩበት የነሐስ ወስከምቶች ነበራቸው፤ እንዲሁም በአራቱ ማእዘኖች የመታጠቢያ ገንዳ መደገፊያዎች ነበሩ፤ መደገፊያዎቹም የአበባ ጉንጉን በሚመስሉ ቅርጾች አጊጠው ነበር።
በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን፥ በኮቦር ወንዝ በምርኮኞች መካከል ነበርሁ፥ ሰማያት ተከፈቱ፥ እኔም የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።
የመንኰራኵሩም መልክና አሠራር የቢረሌ መልክ ይመስል ነበር፥ የአራቱም መልክ አንድ ዓይነት ነበር፥ መልካቸውና አሠራራቸው በመንኰራኵር መካከል ያለ መንኰራኵር ይመስል ነበር።
እኔም አየሁ፥ እነሆ በኪሩቤል አጠገብ አራት መንኰራኵሮች ነበሩ፥ አንድ መንኰራኵር በአንድ ኪሩብ፥ አንድ መንኰራኵር በአንድ ኪሩብ አጠገብ ነበረ። የመንኰራኵሮቹም መልክ የቢረሌ ድንጋይ ይመስል ነበር።