ሕዝቅኤል 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክንፎቻቸው እርስ በእርሱ ይነካካ ነበር፥ ሲሄዱም አይዞሩም፥ እያንዳንዱም ቀጥ ብሎ ይሄድ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክንፎቻቸውም እርስ በርስ ይነካኩ ነበር። እያንዳንዱም ቀጥ ብሎ ይሄድ ነበር፤ ወደ ኋላቸውም ዞር ብለው አይመለከቱም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእያንዳንዱ ፍጥረት ሁለት ክንፎች ግራና ቀኝ ተዘርግተው ጫፎቻቸው ይነካካሉ፤ ስለዚህ ሰውነታቸው ወዲያና ወዲህ ሳይል በኅብረት ይንቀሳቀሱ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሁሉም ክንፎቻቸው አንዱ ከአንዱ ጋር የተያያዘ ነው፤ ሲሄዱም ወዲያና ወዲህ ሳይሉ አቅንተው ይሄዳሉ፤ አንዱም አንዱም ወደፊቱ ይሄዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክንፎቻቸው እርስ በእርሱ የተያያዘ ነበረ፥ ሲሄዱም አይገላምጡም ነበረ፥ እያንዳንዱም ፊቱን አቅንቶ ይሄድ ነበር። |
ፊቶቻቸውም በኮበር ወንዝ ያየኋቸውን ፊቶች ይመስሉ ነበር፥ እነርሱና መልካቸውም እንዲሁ ነበረ፥ እያንዳንዱ ቀጥ ብሎ ወደ ፊት ይሄድ ነበር።
ነገር ግን ወንድሞች ሆይ! ሁላችሁ ተስማምታችሁ በአንድ ልቡና እና በአንድ አቋም በአንድነት የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።